At the Ethiopian Community Association in Nashville (ECAN), we are committed to the economic empowerment of our community. We provide the tools, networking, and professional guidance necessary for individuals to thrive in the workforce. Our goal is to foster financial stability and professional success for all.
በናሽቪል የኢትዮጵያውያን ማህበር (ኢማና) ለማህበረሰባችን ሙያዊ አቅም መጎልበት ቁርጠኞች ነን። ግለሰቦች በስራው ዓለም ስኬታማ እንዲሆኑ አስፈላጊ የሆኑ የክህሎት፣ የግንኙነት እና የሙያ መመሪያዎችን እናቀርባለን። አላማችን ለሁሉም የሙያ ስኬትን ማምጣት ነው።
Are you a professional who wants to give back? Help our community members navigate their career paths.
Free Résumé Preparation Assistance
ECAN provides résumé writing and career preparation workshops to help community members create strong, professional résumés and cover letters. These services can support job seekers in presenting their skills effectively and increasing their confidence during the hiring process.
Job Opportunity Connections and Referrals
ECAN connects members with employment opportunities through partnerships with local employers, workforce agencies, and community organizations. By sharing job openings, referrals, and hiring event information, ECAN can help individuals access meaningful employment and career advancement opportunities.
Internship Opportunities for Youth and Young Professionals
ECAN collaborates with businesses, nonprofits, and educational institutions to create internship opportunities that provide hands-on experience for students and young professionals. These experiences can help participants build practical skills, explore career interests, and strengthen their professional networks.
Mentorship and Professional Networking
ECAN offers mentorship and networking programs that connect students, young professionals, and job seekers with experienced professionals and business leaders. Through career guidance, workshops, and networking events, participants can gain valuable insights, leadership skills, and professional connections.
Workforce Guidance and Career Navigation
ECAN offers workforce development support through career counseling, interview preparation, job readiness training, and educational guidance. These programs can help individuals navigate career pathways, identify training opportunities, and successfully transition into stable employment and professional growth.
የስራ ልምድ/ሬዙሜ ዝግጅት ድጋፍ
ኢማና (ECAN) የማህበረሰቡ አባላት ፕሮፌሽናል የሆነ የስራ ልምድ (Résumé) እና የማመልከቻ ደብዳቤ እንዲያዘጋጁ የአውደ ጥናት ድጋፍ ያደርጋል። ይህም ስራ ፈላጊዎች ብቃታቸውን በሚገባ እንዲያሳዩ እና በቅጥር ወቅት ያላቸውን በራስ የመተማመን መንፈስ እንዲጨምር ይረዳል።
የስራ ዕድል እና ጥቆማ
ከአካባቢው አሰሪዎች እና የስራ ስምሪት ኤጀንሲዎች ጋር በመተባበር አባላትን ከስራ ዕድሎች ጋር እናገናኛለን። ኢማና ግለሰቦች የተሻለ የስራ ዕድል እንዲያገኙ ክፍት የስራ ቦታዎችን ይጠቁማል፤ እንዲሁም የድጋፍ ደብዳቤዎችን ይሰጣል።
ለወጣቶች የልምምድ ስራ ዕድሎች
ኢማና ለተማሪዎች እና ለወጣት ባለሙያዎች የልምምድ ስራ (Internship) ዕድሎችን ለመፍጠር ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር ይሰራል:: ይህም ወጣቶች ተግባራዊ ክህሎት እንዲቀስሙ እና ሙያዊ ትስስር እንዲፈጥሩ ይረዳቸዋል።
የሙያ ምክር እና የኔትወርክ ግንኙነት
ስራ ፈላጊዎችን ተሞክሮ ካላቸው ባለሙያዎች እና የንግድ መሪዎች ጋር እናገናኛለን። በሙያ መመሪያ እና በክህሎት ማሳደጊያ ዝግጅቶች አማካኝነት ተሳታፊዎች ጠቃሚ እውቀቶችን እና የአመራር ብቃትን ያገኛሉ።
የስራ ዝግጅት መመሪያ
ኢማና የሙያ ምክር፣ ለቃለ-መጠይቅ ዝግጅት እና የስራ ዝግጁነት ስልጠናዎችን ይሰጣል። እነዚህ ፕሮግራሞች ግለሰቦች የሙያ መንገዳቸውን እንዲያገኙ እና የተረጋጋ የስራ ህይወት እንዲኖራቸው ይረዳሉ።